February 2020 community update
የማኅበረሰባችን ጎመር አዝመራ
- ማኅበረሰባችን በዳዴ ሲንፏቀቅ ቆይቶ ቀስ በቀስ በእግሩ ለመሄድ ደፋ ቀና እያለ ነው፡፡ ወርቅ በእሳት ይፈተናልእንደሚባለው ላለፉት ሁለት ዓመታት ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ ውጣ ውረዱን ችለው በቦርድና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነትማኅበረሰቡን ሲመሩ የነበሩት አባላት የሥራ ዘመናቸው ስላለቀ የምርጫ ኮሚቴ ተቋቁሞ አዳዲስ እጩ ተመራጮችን በመቀበልላይ ይገኛል፤ ስለሆነም በማኅበረሰቡ ምርጫ መሳተፍ የአባላት መብትና ግዴታ ነው፡፡ ይህን በሚኒሶታ ያለውን ትንሹንኢትዮጵያ – ማኅበረሰቡን – ለማገልገል ማመልከት ወይም ሌላ ብቁ የሆነ አባል ማጨት የሚቻልበትና የሚያስፈልግበት ወቅትአሁን ነው፡
- 124ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በአል ደረሰ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ቋንቋ፣ ብሔርና ሃይማኖት ሳይገድበው እንደንብበመትመም ተዋግቶ ድል አድርጎ የአገሩን ነፃነት በማስከበር ለአፍሪቃና ሌሎች ቅኝ ተገዥ አገሮች የነፃነት ጎህ የቀደደበበት የድልቀን መታሰቢያ ቅዳሜ የካቲት ፳፩ ቀን ፪፲፻፲፪ ዓም (2/28/2020) ስለሚከበር የኢትዮጵያን አርበኞች ተውፊቶች፣ የታሪክምሁራንን ኃይለቃል የምናይበት፣ የምንሰማበትና ለታዳጊው ትውልድ የምናስተላለፍበት ቀን ነው፡፡
- በየዓመቱ በሚኒሶታ ባህላዊ ቅርስ የሚታይባቸው አገራዊ የባህል ትዕይንት (Festival of Nations) ቀኖች አሉ፡፡ዘንድሮም እንደ ተለመደው በሪቨር ሴንተር ሴንትፖል ከተማ ከሚያዚያ ፳፪–፳፭ (4/30/-5/3/2020) ይከበራል፡፡ ስለሆነም የብዙ ብሔር–ብሔረሰብ አገር የሆነችው ኢትዮጵያ ባህላዊ ቅርሷ የሚታይበትና የሕዝቦቿ ሕብርና ውበት ትዕይንት ቀን ስለሆነየአገሩን ባህል ለማሳወቅ የሚፈልግ ዜጋ ሁሉ ያለውን የአገር ቅርስ መዘክር ይዞ ለመምጣት፣ ተራ ገብቶም ለማሳየት በሩ ክፍትበመሆኑ በመመዝገብ ቦታ መያዣው ጊዜ አሁን ነው፡፡
- ማኅበረሰባችን አገልግሎቱን ሰፋ አድርጎ እንዳይቀጥል ካደረጉት ዋና ነገሮች አንዱ ቤት አልባነቱ ስለሆነ ተቋጭቶ ያለቀለትን የማዕከል አስፈላጊነት ሐሳብ እውነት ለማድረግ የሕንፃ ኮሚቴ ተቋቁሞ የዓላማው ደጋፊዎችን በማስተባበር ላይ ስለሚገኝከጎኑ የመሰለፊያው ጊዜ አሁን ስለሆነ በመከታተል ከጎንህ አለን እንድትሉት ይጠብቃል፡፡
- ሌላው የሚኒሶታ ማኅበረሰባችንን ከፍተኛ የደስታ ድባብ ያጠላበት በሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን የሚካሄደው፴፯ኛው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር በመንታ ከተሞቻችን እንዲከናወን መወሰኑ ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ ማኅበረሰባችንዝግጅቱ ወደሚኒሶታ እንዲመጣ ከማድረግ ጀምሮ ጉዳዩን ከሚያስተባብሩት አካላት ጋር ግምባር ቀደም ተሳታፊ ሆኗል፡፡ልዩነታችንን ሁሉ አጥፍቶ ሁላችንንም በአንድ አገር ዜጋነት የሚያስተሣስረን ስፖርት ስለሆነ ለስፖርት ባህሉና ለፌዴሬሽኑ ትልቅክብርና ዋጋ እንሰጣለን፡፡
አገር ወዳድ ሁሉ ደስ ይበለን! እንግዲህ ፈረሱም ይኸው ሜዳውም…ሁላችንም ሠርገኞች ሁላችንም እድምተኞች ነንና በግብረ-ኃይል(Task force) እና በልዩ ልዩ ኮሚቴ አባልነት ሲያገለግሉ እንደቆዩት አባሎቻችን እነዚህን በአገራችንና በኅበረተሰባችን ስም በሚደረጉ ማኅበራዊእንቅስቃሴዎች በአንዱ ወይም በሌላው ውስጥ ተሳትፎ
የመሥራት የውዴታ ግዴታ ወይም በጎ ፈቃደኛነት የሚጠይቅ ስለሆነ ጎበዝቀበቶህን እህት መቀነትሽን ጠበቅ አድርጋችሁ
እንድትሰለፉ ትላለች እናታችሁ::
የማኅበረሰቡ የናንተው ዓለም ማሳያና ማኅበራዊ እሴት ስለሆነ ድርጅቱ የት ደረሰ ከማለት ባሻገር እኔስ ምን አደረኩለት ብሎ ራስን መጠየቅም ተገቢ ስለሆነ
አብ የት? እም የት? ለማኅበረሰቤ ምን ላድርግ? ምን ልታዘዝ? ለምትሉ በጎ ፈቃደኞች ወገኖቻችን ሁሉ አስተባባሪዎች እኝሁላችሁ፡-
አስመረጭ ኮሚቴ
ወ/ሮ እጸገነት ለማ 651 307 0997
ወ/ት ማህሌት 612 600 2838
አቶ መላኩ መላኩ በቀለ 612 618 9715
ሕንፃ ኮሚቴ
ኢንጂነር ግርማ ይስማው 6518083300
አቶ ታደሰ ንጋቱ 651 338 2181
አቶ መስፍን መኮንን 651 233 4490
የአድዋ ድል በዓል ዝጅትና የፌስቲቫል ኦፍ ኔሽን ኮሚቴም ሰሞኑን ይገለጻል፡፡
ለቀሩት ጉዳዮች ሁሉ እንድታገኙን ተከሥተብርሃን ተፈራ ፀሐፊ 651 703 2854
ተስፋዬ እንግዳ ሊቀመንበር 612 517 5429
“ኢትዮጵያዊነት ክብር ነው”