Make your donation to the building committee using the button below
በ2020 መግቢያ ላይ የሕንጻ ኮሚቴው የተለያዩ የገቢ ማስገኛ እቅዶች ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ በመላው ዓለም ላይ የተከፈተው የኮቪድ ፩፱ ወረርሽኝ ያናቆረው እንደሆነ እናስታውሳለን::
ይህም በመሆኑ የሕንጻ ኮሚቴው ለህብረተሰቡ በታህሣስ 7፣ 2019 ስብሰባ ላይ ቃል በገባው መሠረት ተከታታይ ስብሰባ አድርጎ ገለጻ ሊሰጥና ሊያስተባብር ሳይችል ተርቷል፡፡ ሆኖም ግን የሕንጻ ኮሚቴው በወር ሁለት ጊዜ እየተገናኘ ሲወያይ ቆይቶ ውሳኔ ላይ በመድረስ የአመቱ መጨረሻ ውይይትና ገለጻ ለመስጠት ህብረተሰቡን በኢሜልና በቴክስት እንዲሁም በሶሻል ሜዲያ በመጋበዝ በ12/12/2020 በርካታ ሰዎች በተገኙበት ስብሰባውን አካሂዶ ውይይት አድርጎ የሕንጻ ግዢውን ማስተባበር ምን ደረጃ እንዳለ ገለጻ ሰጥቷል፡፡
በአሁኑ ሰአት ሕንጻ ኮሚቴው በጊዜው ሁኔታ በፈለገውና ባቀደው መሠረት ህብረተሰቡን ሰብስቦ ማስተባበርና ማወያየት የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢስያ ፕሮግራሞችን ማድረግ ሳይችል ቀርቷል፡፡ ይሁንና ኮሚቴው በተከታታይ ስብሰባዎችን እየተገናኘ እቅዶች በመንደፍ ልይ ይገኛል፡፡
ይህ የተስፋፈብን የጊዜው በሽታ ሲቃለል ህብረተሰቡን በአካል አግኝተን በማወያየት እንደምናቀናብር እርግጠኛ ነን፡፡
በዚህ ሰአት የሕንጻ መግዣ ለህብረተሰቡ በዶኔሽን እንዲህም በገቢ ማስባሰብ ሂደት የተወሰነ ገንዘብ ቢኖርም ለሕንጻ ግዢ በቂ ባለመሆኑ ብዙ ሥራ ይጠይቃል፡፡
የማህብረሰባችህን ማረፊያና መሰብሰቢያ የሚሆን ሕንጻ ለመግዛት የእያንዳንዳችን የኢትዮጵያውያን እርዳታ አስፈላጊ ነው፡፡
አባል የሆናችሁ እመታዊ ክፍያችሁን በመክፈል ያልተመዘጋብችሁ በመመዝገብ ቸር ልገሳችሁና ስጦታችሁን ለሕንጻው መግዣ በመለገስ የማህብረሰቡን ምኞት ለማሟላት ጥረት እንድታደርጉ እንጠይቃለን
በቀጥታ ለህንጻ መግዢያ ዶኔሽን ማድረግ ብትፈልጉ ከዚህ ሥር በተቀመጠው የሕንጻ ኮሚቴ አካውንቱ ማስገባት ይችላሉ።
ባንኩ Wells Fargo የአካውንቱ ቁጥር 6780621741 ራውቲንግ 091000019 ነው
የሕንጻ ኮሚቴው በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ (ECM) እንዲሁም በማህረሰቡ ስም ለምታደርጉት ሁሉ ምስጋናቸው የከበረ ነው፡፡
“አዎ ማህበረስባችን የኔ የሚለው ፤ምረቃውን ሰርጉን ባህላዊና ታሪካዊ ውይይቱን የሚያካሂድበት፤ ኪንነቱን የሚያስተዋውቅበት፤ የምንማማርበት፤ የምንመክርበት፤ አዲስ የመጡትን የምናለማምድበት ማእከል እንዲኖረን የሕንጻ ኮሚቴው ሥራውን እንደቀጠለ ነው :: ምክራችሁን ድጋፋችሁንና ወቀሳችሁን አትንፈጉን፡፡”
የሕንጻ ኮሚቴ