Advisory board appointment

 In News

ለኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት በሙሉ

ማኅበረሰባችን የት ደረሰ? ከማለት እኔ ለድርጅቱ ማደግ ምን አድርጌያለሁ? በማለት ከጎኑ የመሰለፊያው ጊዜ አሁን ነው። ማኅበረሰባችን ከጊዜ ወደጊዜ ጥቂት በጥቂቱ ወደፊት እየተራመደ ስለሆነ የእድገቱን መጠን የሚወስነውም በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ስለሆነና ማኅበረሰቡን የሚያሰባስብ አንድ የጋራ ማዕከል ማቋቋም እንደሚያስፈልግ የኅብረተሰቡ ፍላጎት መሆኑ ስለታወቀ በኢንጂነር ግርማ ይስማው የሚመራ አምስት አባላት ያሉበት የሕንፃ ኮሚቴ የአጭርና የረዥም ጊዜ ዕቅዶችን ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ቀደም ሲል መግለጻችን ይታወሳል።

ከዚህም በተጨማሪ የሥራ አመራር ቦርዱ ለረዥም ጊዜ ሲከታተል ቆይቶ ማኅበረሰቡ ካለፈው ተሞክሮ በመማር ለወደፊቱ የአመራር ድክመት እንዳያጋጥመው ወይም አንዳች ችግር ቢያጋጥመው በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ X-5 መሠረት ፈጥኖ አማራጭ መፍትሔ የሚፈልግ በዳበረ ሙያና ልምድ የተካኑ አምስት አባላት ያሉት የአማካሪ ቦርድ አቋቁሟል፤ የነዚህን አባላት ዝርዝር ከዚህ በታች እየገለጽን፣ ኅብረተሰቡም ያለውን ገንቢ ሐሳቦች  በ https://ethiopiancommunitymn.org/ ድረገጽ በመስጠት፣ በፈቃደኛነት ማኅበረሰቡን ለማጠናከር ማድረግ የሚፈልገውን አስተዋጽኦ መግለጽ የሚችል መሆኑን በትህትና አናሳውቃለን።

የተመረጡት የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አማካሪ ቦርድ አባላት፡-

  1.  ቄስ ፍራንሲስ እስጢፋኖስ
  2.  ዶክተር አሻግሬ አጥሬ
  3.  አቶ ሙሉጌታ አርዓያ
  4.  አቶ ተፈራ ሽመልስ
  5.  ዶክተር ኤልያስ አያና
Recent Posts
Contact Us

We're not around right now. But you can send us an email and we'll get back to you, asap.