Ethiopia Rehabilitation Fundraiser

 In America, Ethiopia, General, Minnesota, People

እንደወጡ ቀሩ

“ከመልከም ሹቱ መልካም ስም ይበልጣል ይባላል፤ ምክንያቱም ሞት አይቀርም ስም አይቀበርም ነውና”

ውድ ወገኖቻችን! ውድ ኢትዮጵያዊያን!

ሁላችንም እንደምናውቀው በአሁኑ ስዓት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል: በኦሮሚያ፣ በሶማሊያ፣ በጉራ ፈርዳ፣ ኮንሶ፣ በማይካድራና ሌሎችም የኢትዮጵያ ክልሎች በወገኖቻቾን ላይ አሰቃቂ የሆነ ዘርን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፋናመፈናቀል መሰደድ፣ ልጆች ያለ ወላጆቻቸው እንዲሁም ወላጆች አይናቸው እያየ ልጆቻቸውን በሞት ተነጥቀው በገዛሀገራቸው ቀባሪ አጥተው  የሰዎች አስክሬን በየቦታው ከእንሰሳ አንሶ በጅምላ ሃማኖትንና እና ባህልን በተፃረረ መልኩ  በአንድ ጉድጔድ ሲቀበሩ ከማየት የበለጠ የሚዘገንን ነገር ምንድን ንው?

ይህ ሁሉ በወገኖቻችን ላይ በመድረሱ እኛ በውጪ የምንኖር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁምየኢትዮጵያ ወዳጆች ከልብ አዝነናል።

እነዚህን ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም በሚነሶታ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ECM) ሥር  በሕጋዊነት የተመዘገበዉ እናከማኅበረሰቡ ጋር በቅንጅት የሚሠራው ” Ethiopian COVID- 19 and Beyond Relief Organization (ECBRO) እርዳታውን ለማሰባሰብ ኃላፊነት የወሰደ በመሆኑ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና የምንችለውን ሁሉ በማድረግእንድንደርስላቸው በትህትና እንጠይቃለን።

ለዚሁ ዓላማ ተብሎ  በተዘጋጀው gofundme account የዘወትር የደግነት እጃችሁን እንድትዘረጉ እንጠይቃለን። ለመክፈል ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑት፡  https://gf.me/u/zbamvq

በቀጥታ ለመክፈል ለሚፈልጉ የባንክ ሂሣብችን ቁጥር፤ 6112768574

በተረጅዎች ስም እናመሰግናለን

የECBRO ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

Recent Posts
Contact Us

We're not around right now. But you can send us an email and we'll get back to you, asap.